በማጎ ፓርክ ከተገደሉት ስምንት ዝሆኖች ውስጥ የስድስቱ ጥርስ ተወሰዷል

  |   Written by   yonas a   |   ዜና/ news

በ2007 ዓ.ም ቆጠራ ከ175 በላይ ዝሆኖች እንዳሉት የተነገረለት በደቡብ ክልል በሚገኘው የማጎ ብሔራዊ ፓርክ ባለፈው ሳምንት ከተገደሉት ስምንት ዝሆኖች ውስጥ የስድስቱ ጥርስ አንደተወሰደ የፓርኩ ስራ አስኪያጅ ጋናቡል ቡልሚ ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።
ከዝሆኖቹ ግድያ ጋር በተያያዘ ማንም የተያዘ ሰው እንደሌለ ገልፀው አንድ የወረዳ አመራር የነበረ ግለሰብ ግን ዝሆኖቹ ላይ ሲተኩስ እራሱ ቆስሎ ሆስፒታል አንደሚገኝ ገልፀዋል።
ፓርኩ በፀጥታ ሀይሎች ካልተጠበቀ የቀሩ ዝሆኖችም ተመሳሳይ እጣ ሊደርሳቸው ይችላል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ያሉት የዝሆኖች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ መጥቶ በአጠቃላይ ሀገሪቷ ያላት የዝሆኖች ቁጥር ከ,1,000 በታች ሆኗል።
የዝሆኖች ጥርስ በብዛት ለቻይና ገበያ በደላሎች አማካኝነት የሚሸጥ ሲሆን አንዱ የዝሆን ጥርስ እሰከ 1,500 የአሜሪካ ዶላር ለገዢዎች ይሸጣል።

via Fidelpost