አመስጋኝ ትውልድ

  |   Written by   ታመነ መንግስቴ   |   ታሪክ/ historyሀሳቡ የወጣቱ መምህር ሃብታሙ አለማየሁ ነው።እሱ መምህርነትን ለፈጣሪው ፀልዮ እንዳገኘው አጫውቶኛል።አሁን በአዲስ አበባ መካነ አዕምሮ ሁለተኛውን ድግሪ(የአማርኛ አቻዋ ጠፋኝ) እየተማረ እዚያው የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪ ወጣቶችን ያስተምራል።


መምህሩ እንደሚለው የኔና የናንተ ትውልድ የራሱ ቀለም ያስፈልገዋል።ያሳለፈነውን ምዕተ ዓመት(100ዓመት) በትውልድ እርከን  ብንከፋፍለው አሁን ያለነውን ጨምሮ አምስት ትውልድን አቅፏል።ጋሽ ሃብታሙ በሄደበት መከፋፈያ መስመር ለመመስረት ኪነ ጥበብን እነመረኮዛለን።በትውልዶች ጅረት አብረን እንታደም---እስከኛው የምስጋና ትውልድ ድረስ ተከተሉኝ! ሀ.ደባልቄ ትውልድ፦ ዳግማዊ ምኒልክን ተከትለው በነፃዋ ኢትዮጵያ ላይ የራሳቸውን አመክንዮ ለበስ ትውልድ የፈጠሩት የነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝና ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ጅረት አንዱ ነው።በዘመኑ ኢትዮጵያ ከምዕራቡ "ስልጣኔ" ጋር ገና እየተዋወቀች ነበርና እነዚህ ፊታዊራሪ ደራሲና ጠቢባን ድርሻቸው ጉልህ ነበር።

ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ በኢትዮጵያ ቀዳሚው የምጣኔ ሃብት ምሁር ሊያሰኛቸው የሚገባን ስራ ሰርተው ሁለት ጠቃሚና ትውልድ ተሻጋሪ መፅሃፍትን ፅፈው፣ቤተ መንግስት  ውስጥ የነበራቸውን ተቀባይነት በሚያሳይ መልኩ በልጅ ኢያሱ መፈንቅለ መንግስት ላይ የውሸት ወሬ በመንዛት ሳይቀር በጉልህ ተሳትፈው፣"አበጀህ" ተብለው ስልጣንን ለብልጣብልጡ ተፈሪ መኮነን የሗላው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንዲመች አድርገው አልፈዋል።የምዕራቡን ስልጣኔ ከእኛው ጋር እንዲጣመር ይታትሩ ነበር_ደባልቄ።ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ደግሞ በኢትዮጵያ የመጀመሪያፍቃዱን የሚያሰኟቸው ሁለት ነገሮች ላይ ተሳትፈዋል።ዘፈንና መንጃ ፈቃድ።ታሪክ እየተቀረፀ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ አሃዱ ብለው ወደ ኢትዮጵያ ያመጧትን መኪና ቀድመው የነዷት ኢትዮጵያዊ ራሳቸው ንጉሱ ናቸው።መንጃ  አውጥተው ያሽከረከሩበት ግን ተሰማ እሸቴ።ነጋድራሱ የመጀመሪያውን በሸክላ የተቀረፀ ሙዚቃ የዘፈኑት ኢትዮጵያዊም ናቸው። ቅኔያም እንደነበሩም ይነገራል_ደባልቄ።ለ.ድጋፍ ሰጭ፦የዚህ ትውልድ ጠባይ ደጋፊነት ነው።በአብዛኛው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስራዎች ይደመማል፤እሳቸው ያሉትን ቃል ሁሉ እንደ ቅዱስ ይቆጥራል።ንጉሱ ካሉ መፅሐፍ ይፅፋል፣በዓሉ ግርማ "ሀዲስ" የተሰኘ ክሽን ልቦለዱ ላይ እንደፃፈው ይሄ ትውልድ "ቀኃሥ ቤተ ክርስቲያን ተሳለሙ" ብሎ ዜና ይዘግባል።መዘገቡ ነውር ሆኖ ሳይሆን የወሎን ህዝብ ረሃብ ደብቆ መሆኑ ድጋፍ ሰጭነቱን ያስመሰክርበታል።የትውልዱ መሪዎች እነ አቶሁለተኛው ሚካኤልና ብላቴን ጌታ ህሩይወልደ ሥላሴ እንደነበሩ ታሪክ በደማቁ ያትታል።


ክቡር ሊቀ ምሁራን ከበደ ሚካኤል የጃንሆይ ሁለተኛው ፀሃፈ ትዕዛዝ ሊባሉ የሚችሉና ለኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ምግባርን ያጎለበቱ(ያስተማሩ ላለማለት-ምክንያቱም የኢትዮጵያዊያን ምግባር ከዚያ በፊት ቢያንስ 5ሺህ ዓመታትን በፈጀ መሠረት ላይ የቆመ ስለነበረ)፣በንጉሱ ቀኃሥ አማካሪነት ብዙ ተረቶችን የፃፉ፣የመማሪያ መፅሐፍትን ያዘጋጁ፣"ጃፓን እንዴት ሰለጠነችን" ሊያሳዩ የሞከሩ፣የመጀመሪያውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የኪነ ጥበብ ሽልማት የተሸለሙና ከንጉሱ ጋር በነበራቸው የበዛ ግንኙነት በአቻዎቻቸው የሚታሙ_ድጋፍ ሰጭ ነበሩ።ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ ደግሞ በዚያው በቤተ መንግስት ከቀኃሥ ጋር የነበሩ፣ጃንሆይ በማይጨው ጦርነት ተሸንፈው ለንደን ሊሄዱ ሲሉ በተነሳ "ንጉሱ አገር ውስጥ ሆነው ጣሊያንን ይታገሉ" እና" ከአገነበሩ። ሆነው ትግሉን ይቀጥሉ" ክርክር ስደቱን ደግፈው አብረው የተጓዙ፣በዚያው በስደት አገር እንግሊዝ የሞቱ፣ለቀኃሥ የንግስና ዓመት መታሰቢያ ቀን ዋዜማ በሚል የታሪክ መፅሃፍ ፅፈው ርዕሱን "ዋዜማ" ያሉ_ድጋፍ ሰጭ ነበሩ።


ቀጣዩን #አብዮተኛ የተሰኘ ትውልድና ከዋከብቱን ይዠ እመለሳለሁ። እስከዚያ የሚሰማችሁን በ@Tamen1234 አድርሱኝ፤እስከ የእኔና  የእናንተውአመስጋኝ ትውልድ አብረን እንቆይ!