ኮሮና በ አፍሪካ

  |   Written by   ረድኤት የኔነህ   |   ሕብረተሰብ / social
እስካሁን ድረስ መድሀኒት ያልተገኘለት የኮሮና ቫይረስ የሰውን ልጅ እንደ ቅጠል እያረገፈ ይገኛል።በተለይም በአውሮፓ በሽታው የመቀበሪያ ቦታ እስኪጠፋ ድረስ በየቀኑ የሚሞተው ሰው ቁጥር አገግሞ ከሚመለሰው የሰማይ ና የምድር ያህል ተራርቋል።በቫይረሱ በየቀኑ የአያሌ ዜጎቿን ህይወት እየገበረች ያለችው ጣሊያን ከተለያዩ ሀገራት የጤና የባለሙያዎች ድጋፍ እየተደረገላት ቢገኝም አሁንም ግን የሞት መጠኑ እየጨመረ ነው።ጠቅላይ ሚነስትሩ ጁሴፔ ኮንቴም የቻልነው ያህል እየጣርን ቢሆንም ነገሩ ከአቅማችን በላይ ሆኗል ከፈጣሪ ውጪ ይሄን መአት የሚያቆመው የለም ሲሉ ተስፋ እንደቆረጡ የሚያሳይ መልዕክት በማህበራዊ ገፃቸው አጋርተዋል።

#አፍሪካ ;የአለም ግዙፍ የጤና መሠረተ ልማት ባለቤቶቹ አውሮፓውያንን እንዲህ ርህራሄ በሌለው መልኩ ወደ መቃብር እያስገባ የሚገኘው ኮሮና፤ በርካታ ዜጎቿ ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩባት አፍሪካ እንዴት ትቋቋም ይሆን?ንፁህ የመጠጥ ውሃን ለህዝባቸው ማድረስ እንኳ የማይችሉት መንግስታቶች ቫይረሱ አየባሰ ከመጣ እንዴት አድርገው ነው ለዚህ ህዝብ የሚደርሱት የሚለው ጉዳይ ከወዲሁ አስግቷል።

ቫይረሱ አስከ አሁኑ ሰአት ድረስ በ 43 የአህጉሪቱ ሀገራት መግባቱ የተረጋገጠ ሆኗል።አስካሁን የኮሮና ተጠቂ አልተገኘባቸውም የተባሉት አስራ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ብቻ ነው።አነርሱም ከሰሜን- የአህጉሪቱ ክፍል ሊቢያ፣ከደቡብ - ማላዊ፣ኮሞሮስ፣ሌሴቶ፣ቦትስዋና ፤ከምስራቅ -ቡሩንዲ ና ደቡብ ሱዳን፤ከምዕራብ -ሴራሊዮን፣ማሊና ጊኒኒ ቢሳው፤ከማዕከላዊው አፍሪካ ደግሞ ሳኦቶሜ ናቸው።

የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከጥቂት ቀናቶች በፊት "አፍሪካ ክፉ ቀኖች ከፊቷ ተጋርጠዋል"ማለታቸው ይታወሳ።ሰውየው የአፍሪካን የጤና ተቋማት በደንብ ስለሚያቋቸውም ጭምር ነው ይህን ማለታቸው።በተለይም የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ ነበሩም መሆናቸው አይዘነጋም።እናም ነገሮች ከዚህ በላይ ሳይከፉ አፍሪካውያን መዘናጋትን ትተው ይህን ክፉ ጊዜ በጋራ ተባብረው እንዲሻገሩ ከመንግስታቱም በላይ የህዝቡ ጥንቃቄ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል።
#አፍሪካ ኒውስ


ጤና ይስጥልኝ !!!

DNEB commented on 2020-03-22 20:53:36
Well, i don't think its going to be an issue here. we'll see whats in it for Africa.