አዲስ አበባ መካነ አዕምሮ-ማረሚያ ቤት መስሏል

  |   Written by   ታመነ መንግስቴ   |   ሕብረተሰብ / social


በኮሮና ወረርሽኝ የተነሳ ከዛሬ ጀምሮ በሩን የዘጋው አዲስ አበባ መካነ አዕምሮ(ዩኒቨርሲቲ) ተማሪዎቹ የመታገት ስሜት ውስጥ ሲሆኑ አሁን ምሽቱን ለተመለከተው ማረሚያ ቤት መስሏል።

ከበላይ አዛዡ(ፕሬዘደንቱ) ርዕሰ ምሁር ጣሠው ወልደ ሃና ዘንድ በተሠጠ መግለጫ ከዛሬ መጋቢት13 ጀምሮ መውጣትም ሆነ መግባት በተከለከለበት ዋናው ግቢ ውስጥ የተሰባሰበው ተማሪ እጅግ ብዙ ሆኖ ይታያል።

ቤተ መፅሐፉ በአንፃሩ የተማሪ ድርቅ የመታው ሲሆን እኔ በነርኩበት እሁድ ምሽት 1:05 ላይ በዲጅታል አብያተ መፅሐፍ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ከእኔ ጋር 12 ተማሪዎች ይታያሉ።

ግቢው በሰው ተጣቦ ቤተ መፅሐፉ ባዶ መሆኑ አስፈላጊ አይመስለኝም---መፅሐፍት ከጭንቀት የመደበቂያ ሁነኛ አማራጭ መሆናቸውን ከአንድ የምዕራባዊያን ጥናት ላይ ሰምቻለሁ።


።፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ይቆየን!