ደስታ የራቀን ህዝቦች-ኢትዮጵያዊያን

  |   Written by   ታመነ መንግስቴ   |   ዜና/ news


ዛሬ ዓለም በኮሮና ወረርሽኝ የተነሳ ድብርት ውስጥ ሆና ደስታዋን ብትነፈግም ዓለም ዓቀፉ የደስታ ቀን በመሆኑ አንድ ጥናታዊ መረጃ ወጥቶ በመሴ ሪዞርት በኩል ሰምቻለሁ።

በጥናቱ ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ደስታ ከራቃቸው ህዝቦች መደብ የተቀመጥን ሲሆን ከ150 ገደማ አገራት 127ኛ ደረጃን በመያዝ አስቀያሚውን ደስታ አልባነት ባንወድም ታቅፈነዋል።

ደስታ አልባነትን ከገንዘብ፣ስኬት፣መብላት መጠጣት ዓይን ብቻ እንዳንመለከት የሚያደርገን የምድራችን ቱጃር አገራት እነ አሜሪካ በደረጃው ላይ በስካንድብያኑ እነ ፊንላንድ ተቀድመው ስለምናገኛቸው ነው።

ደስታ ከየራሳችን የውስጥ አቅም የሚፈልቅ ለመሆኑ ተደጋግሞ የተነገረ ስለሆነ ልለፈውና ታዋቂው ደራሲና መምህር(በነገራችን ላይ መምህሬ ነው) ኃይለጊዮርጊስ ማሞ በፃፈው "ጥበብ ከጲላጦስ" የተሰኘ ጥልቅ መፅሐፍ ላይ ስለ ደስታ የተባሉ ሁለት የኒል ዶናልድ ዎልሽ ሃሳቦችን ላካፍላችሁ።

ዎልሽ "ከእግዚያብሔር ጋር የተደረገ ውይይት" ብሎ በፃፈው መፅሐፍ ላይ"---ታላቅ ደስታ የሚመጣው ትንንሹን ደስታ አስቀድሞ በመግፋት ነው!" ሲል የዓለሙ ፈጣሪ "የነገረውን" ሃተታ እና"---የምትገኝበትን ቦታ ደስተኛ በማድረግ በዚያ በማድረግ በዚያ ስሜት ውስጥ ትገባለህ እንጅ ለአንተ ተብሎ የተፈጠረ ደስታ የለም።"ብሎ የጨመረለትን እውነታ አጋርቶናል።

ደስታ አይለያችሁ---

።፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ይቆየን!