«ሳይነስ»መንስኤው ለመከላከል የሚጠቅሙ 5 ቀለላልና ተፈጥሮአዊ መንገዶች

  |   Written by   የጠዋት ዜና   |   ጤና / fitness
አንዳንድ ሰዎች የሳይነስ እና የሳይኖሳተስን ልዩነት ሳይገነዘቡ ሳይነስ አለብኝ ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ሳይነስ ሁሉም ሰዎች አላቸው፡፡ይሁን እንጂ የሳይነስ ክፍሎቹ ለበሽታ ሲጋለጡ ሳይኖሳተስ ይባላል፡፡ሳይነሶች የሚባሉት በፊታችን አጥንት ስር የሚገኙ ትናንሽ ክፍት ቦታዎች ሲሆኑ በግንባራችን፣በጉንጫችን፣በአፍንጫችን ውስጥ እና ከአንጎላችን በታች ያሉ ንፁህ እና በአየር የተሞሉ ሳጥኖች ናቸው፡፡

አራት የሳይነስ ዓይነቶች አሉ፡፡

1. ማክስለሪ ሳይነስ - ከልደት ጀምሮ ከሰው ልጅ አካላዊ እድገት ጋር አብሮ የሚያድግ ነው፡፡ይህ የሳይነስ አይነት ከላይኛው የጥርሳችን አካል ማለትም ከመንጋጋችን ጋር ይያያዛል፡፡በመሆኑም የጥርስ ህመም ባለባቸው ሰዎች ላይ በሽታው በቀላሉ ወደ ሳይነስ ሊተላለፍ ይችላል፡፡

2. ፍሮንታል ሳይነስ - የምንለው ደግሞ ከግንባራችን ስር የሚገኝ ነው፡፡ከዚህ ሳይነስ ጀርባ አንጎላችን የሚገኝ ሲሆን ሳይነሱ ከአንጎላችን ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አለው፡፡ ስለዚህ የፍሮንታል ሳይነስ ለህመም ከተጋለጠ አንጎላችንን ለበሽታ የማጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

3. ኤትሞይዳል ሳይነስ - የምንለው መገኛው ከአይናችን ክፍል ጋር ሲሆን የአይናችን ግድግዳ ከኤትሞይዳል ሳይነስ ግድግዳ ጋር ይገናኛል፡፡በመሆኑም የኤትሞይዳል ሳይነስ በበሽታ ከተጠቃ በሽታው በቀጥታ አይናችንን ወይንም አንጎላችንን በቀላሉ ያጠቃል፡፡

4. ስፔኖዳል ሳይነስ - የሚባለው ከልደት ጀምሮ አይኖርም፡፡ነገር ግን ከስምንት ዓመት ጀምሮ ማደግ የሚጀምር የሳይነስ ዓይነት ነው፡፡ይህ ሳይነስ ለአንጎላችን በብዙ አቅጣጫ በጣም ቅርብ ነው፡፡ይህ ሳይነስ በበሽታ ከተጎዳ ለማጅራት ገትር በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል፡፡

የሳይነስ ጥቅሞች ፡-
o ድምፃችን ጥርት ብሎ እንዲወጣ ያደርጋሉ፡፡
o እነዚህ ሳጥኖች ክፍት ወይንም ባዶ ስለሆኑ የራስ ቅላችንን ክብደት ይቀንሳሉ፡፡
o የፊት ቅርፃችን እንዲስተካከልም ያደርጋሉ፡፡

የሳይኖሳተስ በሽታ መንስኤዎች - በአለርጂ፣በኢንፌክሽን፣በእብጠት፣ እጢ እና በአደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡
የሳይኖሳተስ በሽታ ምልክቶች - አፍንጫ በፈሳሽ መታፈን፣የራስ ህመም፣ወፍራም እና ቢጫ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ እንዲሁም ማስነጠስ የመሳሰሉ ምልክቶች ሊኖሩት ይችላል፡፡የሳይኖሳተስ በሽታ በሚከሰት ጊዜ የሳይነሳችን ክፍሎች ፈሳሹን የሚያስወግዱበት ጥቃቅን ቱቦ በመጥበብ መወገድ ያለበት ፈሳሽ እንዲጠራቀም ያደርጋል፡፡በዚህ ጊዜ በእያንዳንዱ የሳይነስ ክፍላችን ላይ ያሉት ቆሻሻ አስወጋጅ አካላት ስራቸውን ባግባቡ መስራት አይችሉም፡፡

ይህንን ህመም ለመከላከል የሚጠቅሙ 5 ቀለላልና ተፈጥሮአዊ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ቀይ ጥሬ ሚጥሚጣ
ቃጠሎን መቋቋም እስከቻሉ ድረስ ሳይኖሳይተስን ለማከም ወደር የማይገኝለት ተፈጥሮአዊ መድሃኒት ነው፡፡አፍንጫን በፍጥነት በማጽዳት ውስጡ ላይ ያለን እብጠት በማጥፋት እፎይታን ይሰጣል፡፡በሚመቾትመንገድ አዘጋጅተው መጠቀም ይችላሉ፡፡

2. ዕርድ
ዕርድ በውስጡ ከርከሚን የሚባል እብጠትና የመለብለብ ስሜትን ሚከላከል ንጥረነገር አለው፡፡ይህ ንጥረነገር ሳይኖሳይተስን ከመከላከሉም በተጨማሪ የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ከፍ ያደርጋል፡፡ 500mg የእርድ ዱቄትን በውሀ በማዋሀድ ወይም በእንክብል መልክ በቀን ሁለት ጊዜ መውሰድ ጠቃሚ ነው፡፡

3. ነጭ ሽንኩርት
ነጭሽንኩርትን በብዛት መመገብ እጅግ በርካታ የጤና ትሩፋቶችን ያስገኛል፡፡በውስጡ አሊሲን የተሰኘ ንጥረነገር የያዘ ሲሆን፣ ይህ ንጥረነገር ቫይረስ ፣ባክቴርያና ፈንገስን የሚከላከል በመሆኑ ለሳይኖሳይተስ ኢንፌክሽን ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡በቀን ውስጥ ከሁለት እስከ ሶስት ራስ ፍሬሽ ነጭ ሽንኩርትን በማንኛውም ዓይነት መመገብ ከፍተኛ ውጤት ያስገኛል፡፡

4. ቀረፋ
በውስጡ ጎጂ የሆኑ ሳይኖሳይተስን የሚያስከትሉ ባክቴርያዎችን የሚገድል ኬሚካል ስላለው ከግማሽ የሻይ ማንኪያ እስከ አንድ የሻይ ማንኪያ ድረስ ከወለላ ማር በመቀላቀል በአንድ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሀ መጠጣት ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡

5. ዝንጅብል
ዝንጅብል በውስጡ ፀረ-የአፍንጫ ፈሳሽ እና ፀረ- መለብለብና እብጠት ኬሚካሎችን በውስጡ ስለያዘ እንዲሁም የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ስለሚጨምር ሳይኖሳይተስን ለመከላከል ይረዳል፡፡ የዝንጅብል ሻይን ከሎሚ ጭማቂ ጋር ቀላቅሎ መጠቀም ለሳይኖሳይተስ ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡

yordanos commented on 2020-09-26 08:51:53
ሁሉንም አድርጊያለዉ ገን እንዲያዉም ብሶብኛል