ወዴት እየሄድን ነዉ

  |   Written by   ethiospeaks   |   ሕብረተሰብ / social
ጥቅምት 13 2012 ጠዋት፣ ተፈጥሮ ካላት አንድም ሳታጎድል አንዳችም ሳትሰስት በረከቷን መስጠት ጀምራለች። የጠዋቱ ፀሀይ ፣ የወፎች ዝማሬ እዉነትም እግዜር በወደደዉ አገር የምንኖር መሆኑን እንጂ ትላንት ሰዎች በፈፀሙት ድርጊት የተደበቀ አልሆነም።

እንዳዉ ሰሞኑን የምንሰማዉን ስናስበዉ ለደቂቃ ዝግ ብለን መራመድ እንዳለብን የሚያሳይ ነዉ። ሞት በቀለለበት ፍቅር በጠፋበት ዘመን ይህችን አገር ተረካቢ ትዉልድ መቅረፅ ማንም ትዝ ያለዉ አይመስልም። ስለፍቅር እና አንድነት ሳይሆን ስለ ብሄርተኝነት እየሰበክናቸው፣ ኢትዬጲያዊ ሳይሆን ኦሮሞ፣ ትግራዋይ፣ አማራ፣ ሲዳሞ ናችሁ ብለን አሳድገናቸዉ፡ ጎሳ ከፍለን እኔ ቄሮ ፣ ነፍጠኛ ነኝ ብለን አሳይተን እጃቸውን ይዘን ተማሪ ቤት እንዲለወጡ መላክ ከሹፈትም በላይ ዝቅጠት ነዉ።

መንገድ በድንጋይ ዘግቶ ልጅ መንገድ እንዲሰራ ማስተማር ፣ አገርን እያሸበሩ አገር ተረካቢ ማፍራት፣ መንደርን እየበጠበጡ ልጅህን አገሩን፣ ሚስቱን፣ ቤተሰቡን እንዲወድ መምከር እርባና ቢስ ልፋት ነው።

ልጄ ምን አይነት ኢትዮጵያ ላይ እንዲኖር እፈልጋለሁ እንበል፣ ተስፋቸዉን እናለምልም፣ አገርን እንገንባ እንጂ እናፍርስ
ቸር ወሬ ያሰማን